ምስክርነቶቻችን ቢፈተሹሳ?

“ሀገሩን ሁሉ በትምህርቱ የሚያስደምም ሰው ራስ ሆቴል አከባቢ ተነስቷል!” የሚል የወዳጆቼ ጉትጎቷ ቀን ከሌት ቢከታተለኝ፣ በአንድ በኩል በርካቶችን ያስደመመውን ትምህርት ለመቋደስ ብሎም ከዚሁ ከአመለጠህ የወዳጆቼ ጉትጎታ ለማምለጥ በሚል ሁለት ልብ ነበር እግሮቼን ያቀናሁት። በእርግጥም በዛች ቀን ብቻ ወዳጆቼን ምን ነካብኝ ያሰኙ አስተምሮቶችን በአይኔ በብረቱ ተመልክቼ ተመልሻለው፤ ዳግም አልተመለስኩም፤ ደግሞም አልመለስም።

የቃላት ጡጫ እና ጉዳቱ

የብእር ሐሳብ ከማይነጥፍባቸው ነገሮች አንዱ የፍቅር ጉዳይ ነውና ዛሬም ስለ ፍቅር እናውጋ። የፍቅር ታሪኮችን ስናደምጥ ደግሞ ተያያዥ ስሜት መውረሩ አይቀርም። አንዳንዱ ታሪክ ልባችንን ጮቤ የሚያስረግጥ ነው፤ የተከፈለው መሥዋዕትነት ‘ብዙ ውኾች’ ፍቅርን ለማጥፋት የፈረጠመ ጡጫ እንደሌላቸው ምስክር ነው (መኀ. 8፥7)። ሌላው ደግሞ ውስጣችን በቁጭት እንዲብሰከሰክ ምክንያት የሚሆን ነው (2 ሳሙ. 13፥1-20)። በስመ ፍቅር አንዳንዶች የተጎነጩትን ጭቆና እና ግፍን ተመልክቶ አለመቆጣት በርግጥም የተባባሪ ያህል ያስቆጥራል።

የኋለኛው ዘመን አሻራ በፍቅር ፍኖት ላይ

የስሜትና የሐሳብ ቁርኝት የፍቅር አካላት ሆነው ይነሣሉ። ያልተነጣጠለ አብሮነታቸውም አንደኛው ከሌለ የሌላው ሕልውና ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርጋል። ለነገሩ፣ ፍቅርን ከተያያዥ ስሜትና ሐሳብ አፋቶ ትርጉም ባለው መልኩ ማሰብስ ማን ይችላል? ተፈቃሪን በምናብ አጣምሮ ራስን ማብገንን ሆነ የመጨረሻዋ ተጠባቂ ሰከንድ አምልጣን ዘላለምን የተቀላቀለች ይመስል በቁንጥንጥ “ውዳችንን” መጠበቃችን በምንስ ይብራራል? በእርግጥም ከፍቅር ጋር ተያይዞ የምናሳየው መሰጠት፣ ሐዘኔታ፣ ቅናት፣ መረበሽ ከስሜትና ከሐሳብ ትሥሥር ጋር ይዛመዳሉ። የስሜቶቻችን እና የሐሳቦቻችን ቁርኝት ከሌሎች ተደምሮ ባዕድነትን ገፎ ተፈቃሪያችን በአንድት የሚገምድ ምስጢር ነው (ዘፍ. 2፥23-24)።

ፍቅርን የመግለጫ መንገዶች

በፍቅር የተጋመዱ ጥንዶች ትሥሥራቸውን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ማንሣታቸው አይቀርም። አንዳንዱ ጥያቄ የሚሰነዘረው ለአፍቃሪው ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ መልስ ከተፈቃሪው ይሻል። ከሚነሡት ጥያቄዎች መካከል አንደኛው “የፍቅር ጥያቄ” ነው። ራሳችንን፣ “በርግጥ አፈቅራታለሁኝ?”፣ “እሷስ ከልቧ ታፈቅረኛለች?” እንላለን። መነሾው ቢለያይም፣ በደስታ መኻል ስንቅር የሚል ጥያቄ እንደ መሆኑ ያስጠላል፤ ያስፈራልም። ሲ. ኤስ. ሊዊስም፣ “ፍቅር በሕይወታችን ካለ ጽኑና ቀጣይ ደስታ ከዐሥሩ የዘጠኙን እጅ ድርሻ ይወስዳል” እንደ ማለቱ ጥያቄው አይናቅም።

ፍቅር ማለምለሚያ

በፍቅር የተጋመዱ ጥንዶች ትሥሥራቸውን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ማንሣታቸው አይቀርም። አንዳንዱ ጥያቄ የሚሰነዘረው ለአፍቃሪው ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ መልስ ከተፈቃሪው ይሻል። ከሚነሡት ጥያቄዎች መካከል አንደኛው “የፍቅር ጥያቄ” ነው። ራሳችንን፣ “በርግጥ አፈቅራታለሁ?”፣ “እሷስ ከልቧ ታፈቅረኛለች?” እንላለን። መነሾው ቢለያይም፣ በደስታ መኻል ስንቅር የሚል ጥያቄ እንደ መሆኑ ያስጠላል፤ ያስፈራልም። ሲ. ኤስ. ሊዊስም፣ “ፍቅር በሕይወታችን ካለ ጽኑና ቀጣይ ደስታ ከዐሥሩ የዘጠኙን እጅ ድርሻ ይወስዳል” እንደ ማለቱ ጥያቄው አይናቅም።

ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ምን ያህል ስጋት ነው?

ላለፉት 18 ወራት ዓለም ትኩረቱን በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ አድርጎ ቆይቷል።በእርግጥ የጦርነቱ ስፋት እና ያደረሰው ቀውስ ለትኩረቱ ሰበብ መሆኑ የሚጠበቅ ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ ግን በተለያዩ አካባቢዎች ብሔር ተኮር ጥቃቶች እንዲሁም መነሻቸውን ሃይማኖት ያደረጉ ግጭቶችም ተስተውለዋል።

በኢትዮጵያ በወንጌላውያን አማኞች ስም እየተበራከቱ የመጡት “ሐሰተኛ ነብያት እና ፓስተሮች”

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ ራሳቸውን ‘ነብይ፣ ፓስተር’ እያሉ በሚጠሩ ሰዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየታዩ ነው።እነዚህ በተከታዮቻቸው ‘ፓስተር’፣ ‘መጋቢ’፣ ‘ነብይ’፣ ‘የእግዚአብሔር ሰው’ ተብለው በሚጠሩ ሰዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገርያ ከሆኑ ቆይተዋል።ጉዳዩ በወንጌል አማኞች ዘንድ ብቻ ሳይሆን ከእምነቱ ውጪ ያሉ ሰዎችም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ትችታቸውን እንዲሰነዝሩ፣ ምን እየሆነ ነው? በማለት አንዲጠይቁ አድርጓል።

እንኳን ተጋጨን!

ቻይኖች ግጭትን የሚመለከት አስደማሚ አባባል አላቸው፤ “ተጋጭታችሁ የማታውቁ ከኾነ አትተዋወቁም” ይላሉ። መጋጨትን ሲያስቡ የሚጎላባቸው ችግር መኾኑ ሳይኾን፣ ተከትሎት የሚመጣው ጥልቅ ትውውቅ እና ትስስር ነው። ቻይኖቹ እውነት አላቸው፤ አያያዙን ላወቀበት እንደ ግጭት ያለ አግባቢ የለም።

የማንን ጥያቄ ልጠይቅ? – Semayawi Thought

በርካቶች ይጠይቃሉ፤ የጥያቄያቸውም መዳረሻ ግን ራሳቸው አይደሉም፡፡ ጉጉታቸውም ሆነ ኳተናቸው ሸልቅቆ መመልከት የሚፈልገው የሌላን ሰው ህይወት ነው፡፡ እንዲያ አይነቱ ፍላጎት በልጓም ተገቶ፣ ከምንም በፊት የራሱን መንገድ እንዲጠበጥብ ሊደረ…

የልጆቾ ወላጅ ማነው? – Semayawi Thought

ርእሴን ያነበበ ሰው፣ “ወዴት ወዴት ነው?” ሊል ይችላል ፡፡ ቀዩኝ! ወዴትም አይደለም፡፡ አሊያም፣ “ስያሜው ራሱ የሚጋጭ ነው፤” በሚል በሰላ ሂስ መጣጥፌን ሊጀመርው ይመርጥም ይሆናል ፡፡ ግድ የለም ጥቂት ታግሳችሁ ስሙኝ፡፡ በአካል ወላጆ…

‹‹ባልንጀራዬ›› ይሰኛል፤ በማኅበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ ‹‹ባልንጀራዬ /Balinjeraye›› በሚል ሥያሜ ይገኛል። ሌላውን እንደራስ የመውደድ እንቅስቃሴ ነው። በአሜሪካዊው አንድሪው ዴኮርት (ዶ/ር) የተመሠረተ እንቅስቃሴ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ፋካሊቲ የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ረዳት ፕሮፌሰር ተካልኝ ነጋ ምሥረታው ላይ አሉበት። ሰላምና